ቡድን ሀ
የታሪክ 3 ርዕስ ምንድነው?
እየሱስን ማጥመቁ
የታሪክ 4 ርዕስ ምንድነው?
ዮሃንስና ሔሮድያዳ
ዮሐንስ ያጠምቅበት የነበረው ወንዝ ስም ማን ይባላል?
ዮርዳኖስ
ዮሐንስ ያስተምር በነበረበት ጊዜ የነበሩት ንጉሥ እና ንግሥት ማን ይባላሉ?
ሄሮድስ እና ሔሮድያዳ
ዮሐንስ ለኢየሱስ "እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?" ሲለው፣ ኢየሱስ ምን አለው?
ፍቀድልኝ።
ዮሐንስ ሳይፈራ ንጉሡን እና ንግሥቲቱን ወደ እነሱ ሄዶ ምን አላቸው?
የምታደርጉት ነገር ስህተት ነው፤ ከዚህ መጥፎ ስራችሁ ተመለሱ።
ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ከሰማይ ምን የሚል ታላቅ ድምፅ ተሰማ?
በእሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው።
የታሪክ 4 መልዕክት ምንድነው?
እኛም እንደ ዮሐንስ ሰዎችን ሳንፈራ ሁልጊዜ ለእውነት የምንቆም ጀግኖች መሆን አለብን።
የታሪክ 3 መልዕክት ምንድነው?
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እኛም እንደ ዮሐንስ ትሁት መሆን አለብን።
ዮሐንስ ስህተታቸውን ስለነገራቸው፤ ንጉሡ ሄሮድስ ዮሐንስን የት አኖረው?
እስር (ወይኒ) ቤት።