ከ12ቱ ደቀ መዛሙርት መካከል
አንዱ ገንዘብ ያዥ ነበር
ታድያ በልቡ ስስት ነግሶ
ጌተውን ሸጠ::
ይሁዳ ነው።
ድር ቢያብር
አንበሳ ያስር
መተባበር መልካም ነው
ኢትዮጲያ በየትኛው የአለማችን አሀጉር ትገኛለች
አፍሪካ
እናቲቱ ጥቁር፣ ልጆቿ ነጫጭ
ጀበናና ሲኒ
እደልቤ ብሎ አምላክ የመርጠው
አንድ መቶ ሀምሳ መዝሙር የደርሰው
የእስራኤል መሪ ይኸ ንጉስ ማነው?
ቅዱስ ዳዊት
የቆጡን አወርድ ብላ
የብብቷን ጣለች
ሌላ ለማግኘት ያለንን ማጥፋት እንደሌለብን
የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
ሀ. ሁልግዜ መፍጠን እና መችኮል አለብን
ለ. በችኮላ መሥራት ውጤት አያመጣልንም
ሐ. በሰንበሌጥ ቤትን መስራት መልካም ነው
መ. ሁሉም መልስ ናቸው
መ. በችኮላ መሥራት ውጤት አያመጣልንም
ጥቁር አዞ ተጠማዞ
መንገድ (አስፋልት)
የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ማን ነው ? የቆረቆሯት ንጉስ ማን ይባላሉ ?
አዲስ አባባ ስትሆን የቆረቆሯት ደሞ ምኒሊክ ።
አራት እግር አለው ግን ወንዝ መሻገር አይችልም
አልጋ / ወንበር / ጠረቤዛ
ሰለ አፄ ምንሊክ የምታውቁትን ተናገሩ
•አዲስ አበባን የቆረቆሩ መሪ ናችው
•ጣልያን ወራሪ የኢትዮጲያን ህዝብ አስተባብረው ያሸነፉ መሪ
•አዲስ አበባ ዘመናዊ ስልክ እና መኪና ያስገቡ መሪ
ቢሄድ ቢሄድ የማይደክመው?
ወንዝ
አፄ ቴዎድሮስ በምን ይታወቃሉ
●ለ ኢትዮጲያ አንድነት የታገሉ መሪ ናቸው
●ከ እንግሊዝ ጦር ጋር የተዋጉ መሪ
ነገርን አዳምጦ እህልን አላምጦ
ሀ. ከመናገራችን በፊት በደንብ ማዳመጥ አለብን
ለ. ማዳመጥ ማለት ማላመጥ ማለት ነው
ሐ. መናገር እንጂ ማዳመጥ አይጠቅምም
መ. ሁሉም መልስ ናቸው
ሀ. ከመናገራችን በፊት በደንብ ማዳመጥ አለብን
ኢትዮጲያ በአለም ከምትታወቅበት ነገር አንዱን ጥቀስ
•የኢትዮጲያ አየር መንገድ
•የሰሜን ተራሮች
•ረጅም ርቀት ሩጫ ውድ ድር
አባ ሲሉት ቆብ የሌለው ምንድን ነው ?
አባ ጨጓሬ
መጽሐፍ ቅዱስ “እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ ከእነዚህም የሚበልጠው _____ ነው፡፡” በተጨማሪም “እግዚአብሄር ____ ነው” ይላል
ፍቅር
ስሄድ ይሄዳል ፣ ስቆም ይቆማል ፣ ስተኛ አፉን ከፍቶ ይተኛል
ጫማ
ኢትዮጵያ የምትገኘው በአፍሪካ ቀንድ ሲሆን የሚያዋስኑዋት ሀገሮች እነማናቸው ?
ሀ. ሱዳን
ለ. ኬንያ
ሐ. ሶማሊያ
መ. ጅቡቲ
ሠ. ሁሉም መልስ ናቸው
ሁሉም መልስ ናቸው
ቢሄድ ቢሄድ የማይደክመው?
ወንዝ