ቀጨኔን ከበስተሰሜን አቅጣጫ ቁልቁል የሚመለከታት ከፍ ያለ ስፍራ ምን ይባላል?
የእንጦጦ ኮረብታ
በሰርግ ምሽት የሙሽራው እናት ለሙሽሪት የምታወጣላት፤ ከዚያም በኋላ በባሏ ቤተሰቦች ዘንድ የምትጠራበት አዲስ ስም ምን ይባላል?
የምራት ስም
አስተዛዛኞች የኃዘንተኞችን ልብሶች ያጥባሉ፣ ፍራሽ ይነሳል፣ ፍራ፟ጅ ተደርጎ የለቅሶው ፍጻሜ ይሆናል። ይህ የሚሆነው በስንተኛው ቀን ነው?
በሰባተኛው ቀን
የሙሽሪትን ድንግልና የሚያረጋግጥ፤ ለቤተሰቧ በዛቅማጦች የሚደርስ የምስራች ሥርዓት ማስመስከሪያ ምን ይባላል?
የደም ሻሽ
ዱባለች፣ ኮምታሬ፣ መነን፣ ሳላይሽ ምንድን ናቸው?
የድርና ማግ ክር አይነቶች
የቀጨኔ አካባቢ መጠሪያ ስሙን ያገኘው በምን መነሻ እንደሆነ ይነገራል?
ከቀጭኔ መኖሪያነት ጋር በተዛመደ
ለሙሽሪት በትዳር ሕይወቷ እንዳትሽኮረመም፤ በመልስ ቀን ምሽት ለሙሽሮች የሚደረግ ድራማዊ ሥርዓት ምን ይባላል?
ጥፍሮዬ/ጥፍሮ በረረ
በአደጋ፣ በሌብነት፣ በእሳት ወይም በሌላ ችግር ለተጎዳ ሰው ማኅበረሰቡ የአቅሙን ገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ የሚያደርግበት ወንፈል ምን ይባላል?
ግቡልኝ
ሙሽሮች ከሰርጋቸው በኋላ በዘመዶቻቸው ቤት በየተራ እየተጠሩ የሚታደሙበትና የሚጋበዙበት ሥርዓት ምን ይባላል?
ቤት-ማያ
ከስንዴ እና ጤፍ የሚዘጋጅ ቀጠን ያለ አነባበሮ ምን ይባላል?
አይነብሩት
በራስ-አገዝ የተሰሩት የመጀመሪያዎቹ የቀጨኔ አስፓልቶች በምን መልኩ ተጠሩ?
፩ኛው፣ ፪ኛው፣ ፫ኛው መንገድ
ሴት ሽማግሌዎች ወደ እጩ ሙሽሪት ቤተሰቦች ዘንድ በመሄድ "ልጃችሁን ለልጃችን" በማለት የሚፈጽሙት የማጨት ሥርዓት ምን ይባላል?
እንጀራ ቆረሳ
ለማስለቀስ በምትቀጠር ሴት አማካኝነት ሀዘንተኛው ሀዘኑ ከውስጡ እንዲወጣ በግጥሞች ማስለቀስ ምን ይባላል?
ሙሾ ማውረድ/ማርገድ
ለአንድ ለትዳር የደረሰ ልጅ ለጋብቻ ተስማሚ የሆነችን ሴት የምትጠቁም እና ጋብቻው እንዲፈጸም የምታደርግ ሴት ምን ትባላለች?
አማጭ
[አማጭን አንድም በጦር፣ አንድም መጦር]
አብይ ጾም እንደገባ በመጀመሪያው ቀን ቤት እና ዕቃዎችን የማፅዳት ሥርዓት ምን ይባላል?
የቅድስት ሥርዓት
ቀጨኔ በቀድሞ ነዋሪዎቿ ዘንድ ማን ተብላ ትጠራ ነበር?
የጥበብ ከተማ
ትልቅ ወንጀል የሰራ ወንጀለኛ የሚቆራኝበት የብረት ሰንሰለትን ተምሳሌት፤ በማድረግ በሙሽሮች አንገት ዙሪያ የሚታሰር
ጃንጅር
የሴቶችን ዳና ተከትሎ፤ የወንድ ሽማግሌዎች የጋብቻውን ቀን የሚወስኑበትና የ'መድረስ' ገንዘብ የሚያስረክቡበት ሥርዓት ምን ይባላል?
ነገር ቁርጫ
ልጃገረዶች ተቧድነው፤ አንዷ ግንድ ተደግፋ ትቆምና ሌሎቹ ወገብ ለወገብ ተቆላልፈው፤ እነዚያኞቹ እየዘለሉ የሚፈናጠጡበት ጨዋታ ምን ይባላል?
ሾርሾሬ
በትዳራቸው ፀንተው የቆዩ፣ ያልተፋቱ እና ለማህበረሰቡ ምሳሌ የሆኑ ጥንዶች ወይም ባለትዳሮች ምን ይባላሉ?
የአሚን ባልና ሚስት
ሴቶች በማኅበረሰባቸው ውስጥ ጋብቻ ላይ እንደ ወንዶች ለመወሰን ያላቸውን ከፍተኛ ሚና የሚያሳየውን ምሳሌያዊ አነጋገር ጥቀሱ።
ሴት ታውቅ በወንድ ያልቅ
በፋሲካ ሰሞን ልጃገረዶች እየዘለሉ በሁለት እግራቸው መቀመጫን በመምታት የሚጫወቱት ጨዋታ ምን ይባላል?
ቅርጢፋት