ዐቢይ ጾም
ጸሎት ወስግደት
ነገረ እግዚአብሔር
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ልዩ ልዩ
100

ዐቢይ ጾም ማን የጾመው ፆም ነው?

ሀ. ሐዋርያት             ለ. የነነዌ ሰዎች        

ሐ. ቅዱሳን ነቢያት     መ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ     

መ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

100

ጸሎት ምን ማለት ነው?

ሀ. ምስጋና                ለ. ልመና  

ሐ. ከእግዚአብሔር ጋር ይምንገናኝበት     መ. ሁሉም

መ. ሁሉም

100

ነገረ እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ. ስለ እግዚአብሔር መማር   ለ. ስለ መላዕክት መማር   

ሐ. ስለ ቅዱሳን መማር         መ. ስለ እመቤታችን መማር

ሀ. ስለ እግዚአብሔር መማር

100

አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት በማን አብሳሪነት ነው?

ሀ. ቅዱስ ፋኑኤል       ለ. ቅዱስ ሚካኤል

ሐ. ቅዱስ ኡራኤል      መ. ቅዱስ ገብርኤል

ለ. ቅዱስ ሚካኤል  

100

አሁን ያለንበት እና የምንገለገልበት ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ስሙ ማን ይባላል?

የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን

200

አባታችን ቅዱስ ያሬድ ዓይን ይጹም፣ ጆሮ ይጹም፣ አፍ ይጹም ሲል ምን ማለቱ ነው?

ዓይን ክፉ ከማየት ይጹም፣ ጆሮ ክፉ ከመስማት ይጹም፣ አፍ ክፉ ነገር ከመናገር ይጹም ማለቱ ነው

200

በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በቀን ውስጥ ስንት የጸሎት ጊዜያት አሉ?

 ሀ. 3          ለ. 5

 ሐ. 12       መ. 7

 መ. 7

200

እግዚእ ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ. ጌታ         ለ. ገዢ                

ሐ. ባርያ.     መ. ሀ እና ለ

መ. ሀ እና ለ

200

የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደት ቀን መቼ ነው?

ሀ. መጋቢት 5        ለ. ታኅሳስ 19

ሐ. ታኅሣሥ 24     መ. ግንቦት 12

ሐ. ታኅሣሥ 24

200

ከንዋያተ ቅዱሳት መካከል 3ቱን ጥቀሱ?

ጻሕል፣ እርፈ መስቀል፣ አጎበር፣ ማህፈዳት፣ ሙዳይ፣ ጽንሐሕ፣ መሶበወርቅ፣ ደውል መጥቅእ፣ ቃጭል፣ አትሮኖስ፣ መቅረዝ፣ ታቦት፣ መንበር፣ ልብሰ ተክህኖ፣ ጸናጽል፣ ከበሮ

300

በኒቆዲሞስ ሳምንት የሚታሰበው ማን ነው?

ኒቆዲሞስ

300

ከሦስቱ የስግደት ዓይነቶችን ሁለቱን ይግለጹ

የአምልኮ ስግደት፣ የጸጋ ስግደት እና የአክብሮት ስግደት

300

አብ ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ. ልጅ       ለ. መንፈስ           

ሐ. አባት    መ. ሀ እና ለ

ሐ. አባት

300

ለአባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወላጆቻቸው ያወጡላችው ስም ማን ነው? 

ሀ. ፍሥሐ               ለ. ተክለ ሃይማኖት   

ሐ. ፍሥሐ ጽዮን      መ.  ሀ እና ለ.

ሐ. ፍሥሐ ጽዮን

300

ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት መካከል 4ቱን ጥቀሱ?

ምስጢረ ሥላሴ ፤ ምስጢረ ሥጋዌ ፤ ምስጢረ ጥምቀት ፤ ምስጢረ ቁርባን ፤ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን

400

ከመፃጉዕ ቀጥሎ ያለው እሑድ ምን ተብሎ ይጠራል?

 ሀ. ገብርኄር        ለ. ደብረ ዘይት

 ሐ. ኒቆዲሞስ     መ. ምኩራብ

ለ. ደብረ ዘይት

400

በቀትር (ስድስት ሰዓት) 12PM የምንጸልየው ለምንድን ነው?

ሀ. አባታችን አዳም ዕፀ በልስ በልቶ ከክብሩ የተዋረደበት ሰዓት ነውና እኛም ወደ ፈተና እንዳንገባ        

ለ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ሰዓት ለማሰብ

ሐ. ሰውነታችን የሚደክምበት ሰዓት ስልሆነ እና አጋንንት የሚበረቱበት ሰዓት ስልሆነ በርትተን እንጸልያለን    

መ. ሁሉም

ሐ. ሰውነታችን የሚደክምበት ሰዓት ስልሆነ እና አጋንንት የሚበረቱበት ሰዓት ስልሆነ በርትተን እንጸልያለን

400

ሔር ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ. ቸር            ለ. ደግ   

ሐ. ለጋስ         መ. ሁሉም 

ሀ. ቸር

400

የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የፅንሰታቸው በዓል መቼ ነው? 

ሀ. መጋቢት 24        ለ. ኅዳር 24

ሐ. ታኅሳስ 24         መ. ግንቦት 12

ሀ. መጋቢት 24

400

ከአሥርቱ ትዕዛዛት መካከል 3ቱን ጥቀሱ?

1. ‹‹ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፡፡ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስልለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፤ አታምልካቸው ›› ዘጸ. 20፥2-6

2. ‹‹ የእግዚአብሔር የአምላክን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ ›› ዘጸ. 20፥7

3. ‹‹ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ /አክብረውም/ ›› ዘጸ. 20፥8

4. ‹‹ አባትህንና እናትህን አክብር ›› ዘዳ. 20፥12

5. ‹‹ አትግደል ›› ዘጸ. 20፥13

6. ‹‹ አታመንዝር ›› ዘጸ. 20፥14

7. ‹‹ አትስረቅ ›› ዘጸ. 20፥15

8. ‹‹ በሐሰት አትመስክር ›› ዘጸ. 20፥16

9. ‹‹ የባልንጀራህን ንብረት አትመኝ ›› ዘጸ. 20፥17

10. ‹‹ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ›› ዘሌ. 19፥18

500

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ለስንት ቀን እና ሌሊት ጾመ?

ለአርባ ቀን እና አርባ ሌሊት ጾመ

500

ከሦስቱ የስግደት አፈጻጸም ሁለቱን ዓይነቶች ይግለጹ

1. አስተብርኮ ስግደት - በጉልበት ወድቆ ግንባር መሬት ሳይነካ የምንነሳው ስግደት ነው

2. አድንኖ ስግደት - ራሥን፣ ግንባርን፣ አንገትን ዝቅ በማድረግ የሚሰገድ ነው 

3. ወዲቅ (ሰጊድ) - ሙሉ በሙሉ በጉልበት ወድቆ በግንባር መሬት ነክቶ ምንነሳው ስግደት ነው

500

የእግዚአብሔር ባሕርይውን የሚያውቅ የለም ስንል ምን ማለታችን ነው? 

ሀ. አይመረመርም                        ለ. ይመረመራል

ሐ. ተመራምረን እንደርስብታልን     መ. ሁሉም                   

ሀ. አይመረመርም

500

በግንቦት 12 የሚከበረው አባታችን በዓል ምንድነው?

ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው

500

ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት መካከል ስለ ተዋሕዶ፣ ስለ አምላክ ሰው መሆን የምንማርበት ምሥጢር የቱ እንደሆነ ግለጹ?

ምስጢረ ሥጋዌ

M
e
n
u