ዐቢይ ጾም ማን የጾመው ፆም ነው?
ሀ. ሐዋርያት ለ. የነነዌ ሰዎች
ሐ. ቅዱሳን ነቢያት መ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
መ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ጸሎት ምን ማለት ነው?
ሀ. ምስጋና ለ. ልመና
ሐ. ከእግዚአብሔር ጋር ይምንገናኝበት መ. ሁሉም
መ. ሁሉም
ነገረ እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ስለ እግዚአብሔር መማር ለ. ስለ መላዕክት መማር
ሐ. ስለ ቅዱሳን መማር መ. ስለ እመቤታችን መማር
ሀ. ስለ እግዚአብሔር መማር
አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት በማን አብሳሪነት ነው?
ሀ. ቅዱስ ፋኑኤል ለ. ቅዱስ ሚካኤል
ሐ. ቅዱስ ኡራኤል መ. ቅዱስ ገብርኤል
ለ. ቅዱስ ሚካኤል
አሁን ያለንበት እና የምንገለገልበት ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ስሙ ማን ይባላል?
የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
አባታችን ቅዱስ ያሬድ ዓይን ይጹም፣ ጆሮ ይጹም፣ አፍ ይጹም ሲል ምን ማለቱ ነው?
ዓይን ክፉ ከማየት ይጹም፣ ጆሮ ክፉ ከመስማት ይጹም፣ አፍ ክፉ ነገር ከመናገር ይጹም ማለቱ ነው
በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በቀን ውስጥ ስንት የጸሎት ጊዜያት አሉ?
ሀ. 3 ለ. 5
ሐ. 12 መ. 7
መ. 7
እግዚእ ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ጌታ ለ. ገዢ
ሐ. ባርያ. መ. ሀ እና ለ
መ. ሀ እና ለ
የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደት ቀን መቼ ነው?
ሀ. መጋቢት 5 ለ. ታኅሳስ 19
ሐ. ታኅሣሥ 24 መ. ግንቦት 12
ሐ. ታኅሣሥ 24
ከንዋያተ ቅዱሳት መካከል 3ቱን ጥቀሱ?
ጻሕል፣ እርፈ መስቀል፣ አጎበር፣ ማህፈዳት፣ ሙዳይ፣ ጽንሐሕ፣ መሶበወርቅ፣ ደውል መጥቅእ፣ ቃጭል፣ አትሮኖስ፣ መቅረዝ፣ ታቦት፣ መንበር፣ ልብሰ ተክህኖ፣ ጸናጽል፣ ከበሮ
በኒቆዲሞስ ሳምንት የሚታሰበው ማን ነው?
ኒቆዲሞስ
ከሦስቱ የስግደት ዓይነቶችን ሁለቱን ይግለጹ
የአምልኮ ስግደት፣ የጸጋ ስግደት እና የአክብሮት ስግደት
አብ ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ልጅ ለ. መንፈስ
ሐ. አባት መ. ሀ እና ለ
ሐ. አባት
ለአባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወላጆቻቸው ያወጡላችው ስም ማን ነው?
ሀ. ፍሥሐ ለ. ተክለ ሃይማኖት
ሐ. ፍሥሐ ጽዮን መ. ሀ እና ለ.
ሐ. ፍሥሐ ጽዮን
ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት መካከል 4ቱን ጥቀሱ?
ምስጢረ ሥላሴ ፤ ምስጢረ ሥጋዌ ፤ ምስጢረ ጥምቀት ፤ ምስጢረ ቁርባን ፤ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን
ከመፃጉዕ ቀጥሎ ያለው እሑድ ምን ተብሎ ይጠራል?
ሀ. ገብርኄር ለ. ደብረ ዘይት
ሐ. ኒቆዲሞስ መ. ምኩራብ
ለ. ደብረ ዘይት
በቀትር (ስድስት ሰዓት) 12PM የምንጸልየው ለምንድን ነው?
ሀ. አባታችን አዳም ዕፀ በልስ በልቶ ከክብሩ የተዋረደበት ሰዓት ነውና እኛም ወደ ፈተና እንዳንገባ
ለ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ሰዓት ለማሰብ
ሐ. ሰውነታችን የሚደክምበት ሰዓት ስልሆነ እና አጋንንት የሚበረቱበት ሰዓት ስልሆነ በርትተን እንጸልያለን
መ. ሁሉም
ሐ. ሰውነታችን የሚደክምበት ሰዓት ስልሆነ እና አጋንንት የሚበረቱበት ሰዓት ስልሆነ በርትተን እንጸልያለን
ሔር ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ቸር ለ. ደግ
ሐ. ለጋስ መ. ሁሉም
ሀ. ቸር
የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የፅንሰታቸው በዓል መቼ ነው?
ሀ. መጋቢት 24 ለ. ኅዳር 24
ሐ. ታኅሳስ 24 መ. ግንቦት 12
ሀ. መጋቢት 24
ከአሥርቱ ትዕዛዛት መካከል 3ቱን ጥቀሱ?
1. ‹‹ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፡፡ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስልለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፤ አታምልካቸው ›› ዘጸ. 20፥2-6
2. ‹‹ የእግዚአብሔር የአምላክን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ ›› ዘጸ. 20፥7
3. ‹‹ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ /አክብረውም/ ›› ዘጸ. 20፥8
4. ‹‹ አባትህንና እናትህን አክብር ›› ዘዳ. 20፥12
5. ‹‹ አትግደል ›› ዘጸ. 20፥13
6. ‹‹ አታመንዝር ›› ዘጸ. 20፥14
7. ‹‹ አትስረቅ ›› ዘጸ. 20፥15
8. ‹‹ በሐሰት አትመስክር ›› ዘጸ. 20፥16
9. ‹‹ የባልንጀራህን ንብረት አትመኝ ›› ዘጸ. 20፥17
10. ‹‹ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ›› ዘሌ. 19፥18
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ለስንት ቀን እና ሌሊት ጾመ?
ለአርባ ቀን እና አርባ ሌሊት ጾመ
ከሦስቱ የስግደት አፈጻጸም ሁለቱን ዓይነቶች ይግለጹ
1. አስተብርኮ ስግደት - በጉልበት ወድቆ ግንባር መሬት ሳይነካ የምንነሳው ስግደት ነው
2. አድንኖ ስግደት - ራሥን፣ ግንባርን፣ አንገትን ዝቅ በማድረግ የሚሰገድ ነው
3. ወዲቅ (ሰጊድ) - ሙሉ በሙሉ በጉልበት ወድቆ በግንባር መሬት ነክቶ ምንነሳው ስግደት ነው
የእግዚአብሔር ባሕርይውን የሚያውቅ የለም ስንል ምን ማለታችን ነው?
ሀ. አይመረመርም ለ. ይመረመራል
ሐ. ተመራምረን እንደርስብታልን መ. ሁሉም
ሀ. አይመረመርም
በግንቦት 12 የሚከበረው አባታችን በዓል ምንድነው?
ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው
ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት መካከል ስለ ተዋሕዶ፣ ስለ አምላክ ሰው መሆን የምንማርበት ምሥጢር የቱ እንደሆነ ግለጹ?
ምስጢረ ሥጋዌ