የበገና ታሪክ
የበገና አካል ክፍል
ዜማ
ቅኝት
አገልግሎት
100

በገና ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በማን አማካኝነት ነው?

ሀ. በአጼ ኃይለሥላሴ 

ለ. በአጼ ቴዎድሮስ

ሐ. በቀዳማዊ ምኒሊክ 

ሐ. በቀዳማዊ ምኒሊክ

100

በመንፈስ ቅዱስ የሚመሰለው የበገና አካል ክፍል ''ጌጥ'' ይባላል።


          ሀ. እውነት        ለ.  ሐሰት

  ለ. ሐሰት

        በመንፈስ ቅዱስ የሚመሰለው መቃኛ ነው

100

የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልቶች የሚባሉት ስንት ናቸው? ስማቸው ማን ማን ይባላል?

      3(ሶስት) ናቸው።

                   እነሱም ግዕዝ፣ ዕዝል እና አራራይ

100

የአንቺ ሆዬ ቅኝት ድምጽ በ''C" ሜጀር ሲነሳ

ሀ. C   D   F   G   A    C

ለ. C   D   F   F#   G   C

ሐ.C   C#   F   F#   A   C

መ.C   D   E   G   A   C

ሐ. C   C#   F   F#   A   C

100

በገና ከመደርደራችን በፊት ማደረግ ካሉብን ነገሮች ሁለቱን ጥቀሱ

1 አለባበሳችንን ማስተካከል

2 ጸሎት ማድረግ

3 አቀማመጣችንን ማስተካከል

4 በገናችንን በአግባቡ መያዝ

200

ከሚከተሉት ውስጥ የበገና ትርጉም ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ነዘረ

ለ. መታ

ሐ. ደረደረ

መ. መልሱ የለም

        መ. መልሱ የለም

200

__________ በተጋድሎ ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ይመሰላል።

       

          እንዚራ

200

pentatonic የምንለው ባለ 7 ድምጽ ነው

ሀ. እውነት

ለ. ሐሰት

ለ. ሐሰት

200

የአንቺ ሆዬ ቅኝት የድምጽ ርቀት 1/2፣ 2፣ 1/2፣ 11/2፣ 11/2 ነው


ሀ. እውነት     

ለ. ሐሰት

ሀ. እውነት

200

መዝሙር ለማን ለማን ሊቀርብ ይችላል?

ሀ. ለእግዚአብሔር                            ሐ. ለቅዱሳን መካናት

ለ. ለቅዱሳን መላዕክት እና ሰማዕታት            መ. ለሰንበት 

ሠ. ሁሉም መልስ ነው።





    ሠ. ሁሉም መልስ ነው።

300

ከበገና ጥቅሞች የሚመደበው የቱ ነው?

ሀ. ምስጋና ለማቅረብ                  መ. ትንቢትን ለመናገር

ለ. እርኩስ መንፈስን ለማራቅ          ሠ. ሁሉም መልስ ነው

ሐ. ታቦትን ለማጀብ


ሠ. ሁሉም መልስ ነው

300

በሐዲስ ኪዳን የሚመሰለው የበገና አካል ክፍል የቱ ነው?

   

       የግራ ምሰሶ

300

በድምጾች መካከል ያለው የድምጽ ርቀት መለኪያ ምን ተብሎ ይጠራል?

ቶን (Tone)

ምሳሌ፡ C   D በእነዚህ ድምጽ መካከል ያለው ርቀት 1T (አንድ ሙሉ ድምጽ)

       C   C#  በእነዚህ ድምጽ መካከል ያለው ርቀት 1/2T (ግማሽ ድምጽ)

300

1፣ 1፣ 11/2፣ 1፣ 11/2  ይሄ የየትኛው የቅኝት የድምጽ ርቀት (ቀመር) ነው?

ሀ. የሰላምታ

ለ. የትዝታ

ሐ. የአንቺ ሄዬ

ለ. የትዝታ

300

ከሚከተሉት ውስጥ የዜማ መሳሪያ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ከበሮ                              መ. በገና 

ለ. መቋሚያ                          ሠ. መልሱ የለም

ሐ. ዋሽንት

   

    ሠ. መልሱ የለም

የተጠቀሱት ሁሉም የዜማ መሳሪያ ናቸው።

400

በገና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሶ የምናገኘው በየትኛው ክፍል ነው?

     ሀ. በብሉይ ኪዳን                          

     ለ. በሐዲስ ኪዳን

     ሐ. በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን

     መ. በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጠቀሰም

        

        ሐ. በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን

400

በገና በሁለት መልኩ ልንደረድር እንችላለን። አንዱ በእጃችን (በጣታችንን) ሲሆን ሁለተኛውን በምን ልንደረድር እንችላለን? ምሳሌነቱስ ምንድነው?

 በድህንጻ

ምሳሌነቱም የክርስቶስ ምሳሌ ነው  

400

አንድን ድምጽ በግማሽ ለመቀነስ የሚያስችለን #(ሻርፕ) ይባላል።

ሀ. እውነት

ለ. ሐሰት

ለ. ሐሰት

በግማሽ ለመቀነስ የሚያስችለን b(flat) ተብሎ ይጠራል

በግማሽ ደግሞ ለመጭመር የሚያስችለን #(ሻርፕ) ይባላል

400

ሰላምታ ቅኝት ከተፈጥሮአዊው ቅኝት(Basic Sounds) ስንተኛውን እና ስንተኛውን ስናወጣ ነው የምናገኘው?


3ኛውን እና 7ኛውን

ሰባቱ ድምጾች  - C   D   E   F   G   A   B   C 

   3ኛው   E

   7ኛው    B

ሲወጣ - C     D      F     G     A    C 




   

400

ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ የተጀመረው በቅዱስ ያሬድ ጊዜ ነው?

ሀ. እውነት                 ለ. ሐሰት

ለ. ሐሰት


እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ በፊት ባህሪው ባህሪውን ያመሰግን እንደነበር በዮሐ፡- 17 - 5 

500

የሰው ልጅ በገናን መጠቀም ከጀመረ ለስንት ዓመታት ይሆናል?

ሀ. ከ5816 ዓመት በላይ

ለ. ከ300 ዓመት  በላይ

ሐ. ከ1900 ዓመት በላይ

መ. ከ20 ዓመት በላይ


     ሀ. ከ5816 ዓመት

500

በገናችን ላይ ከድምጽ ሳጥኑ ጀርባ ያለው ቅርጽ የምን ምልክት ነው? ምሳሌነቱስ ምንድነው?  

ምልክቱ ''የመስቀል ምልክት ነው" 

ምሳሌነቱ ዳዊት ከሳኦል ጦር የዳነበት

500

የቤተክርስቲያን የዜማ መሳሪያዎች አከፋፈል - በገና አውታር ካላቸው መሳሪያዎች ጋር የሚመደብ ነው

ሀ  እውነት

ለ  ሐሰት

ሀ. እውነት

የዜማ መሳሪያዎች በ 3 ይከፈላሉ

1. አውታር ያላቸው፦ በገና፣ መሰንቆ

2. በእስትንፋስ የሚነፉ ፦  ዋሽንት፣ መለከት

3. እርስ በርስ በማማታት የሚሰሩ፦ ከበሮ እና ጸናጽል

500

የትዝታ ቅኝት ከ''F'' ሜጀር ስንነሳ የምናገኘው ድምጽ

ሀ.   F   G  A  C   Db  F

ለ.   F   G  AC  D   F

ሐ.  F   G  A  C   D   F


ሐ.  F   G  A  C   D   F

500

በገና ከእንስሳት እና ከእጽዋት ተዋጽኦ ማለትም ከእንስሳት፦ ከበግ (ከበሬ) አንጀት፣ ከቆዳ፣ ከቀንድ እንዲሁም ከእጽዋት ደግሞ ከዋንዛ፣ ዝግባ እንጨቶች የሚሰራ ነው።   ከእንስሳት ተዋጽኦ እና ከእጽዋት የሚሰሩት የበገና አካል ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?

ከእጽዋት፦ 

            ቀንበር(ጋድም)፣ የድምጽ ሳጥን፣ በርኩማ፣ መቃኛ እና መወጠሪያ

ከእንስሳት ተዋጽኦ፦ አውታር፣ እንዚራ፣ የድምጽ ሳጥኑ ልብስ፣ 

                   የመወጠሪያ ማሰሪያ፣  ድህንጻ