''በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:16 ለ. ዘፀ 20: 12 ሐ. ዘፀ 20:8
ሀ. ዘፀ 20:16
''የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:7 ለ. ዘፀ 20: 20 ሐ. ዘፀ 20:18
ሀ. ዘፀ 20:7
''አትግደል'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 4ኛው ለ. 5ኛው ሐ.7ኛው
ለ. 5ኛው
''አታመንዝር'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 5ኛው ለ. 4ኛው ሐ. 6ኛው
ሐ. 6ኛው
ላኤል አባቱ ውሃ አምጣልኝ ሲለው እሺ ብሎ ውሃ አመጣለት። ላኤል የትኛውን ትዕዛዝ ነው ያከበረው?
አባትህን እና እናትህን አክብር
''የሰንበትን ቀን አክብር'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:16 ለ. ዘፀ 20: 8 ሐ. ዘፀ 20:6
ለ. ዘፀ 20: 8
''የሰንበትን ቀን አክብር'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:7 ለ. ዘፀ 20: 3 ሐ. ዘፀ 20:8
ሐ. ዘፀ 20:8
''የሰንበትን ቀን አክብር'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 4ኛው ለ. 3ኛው ሐ.6ኛው
ለ. 3ኛው
''የባልንጀራህን ቤት አትመኝ'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 8ኛው ለ. 10ኛው ሐ. 9ኛው
ሐ. 9ኛው
ማዕዶት እግዚአብሔርን በፍፁም ልቧ ታመልካለች።
የትኛውን ትዕዛዝ ነው ያከበረችው?
ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ የሚለውን
''ከእኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:3 ለ. ዘፀ 20: 8 ሐ. ዘፀ 20:6
ሀ. ዘፀ 20:3
''አባትህን እና እናትህን አክብር'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:7 ለ. ዘፀ 20:12 ሐ. ዘፀ 20:8
ለ. ዘፀ 20:12
''በሐሰት አትመስክር'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 6ኛው ለ. 8ኛው ሐ. 7ኛው
ለ. 8ኛው
''ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 10ኛው ለ. 9ኛው ሐ. 8ኛው
ሀ. 10ኛው
በናያስ በፀሎት እና በመዝሙር ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራል።
የትኛውን ትዕዛዝ አከበረ?
የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ የሚለውን
''አትግደል'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:13 ለ. ዘፀ 20: 8 ሐ. ዘፀ 20:6
ሀ. ዘፀ 20:13
''አታመንዝር'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:13 ለ. ዘፀ 20: 8 ሐ. ዘፀ 20:14
ሐ. ዘፀ 20:14
''ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 1ኛው ለ. 3ኛው ሐ. 2ኛው
ሀ. 1ኛው
''አትስረቅ'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 7ኛው ለ. 9ኛው ሐ. 8ኛው
ሀ. 7ኛው
ኢዮአስ እሑድ ቀን ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ያስቀድሳል።
የትኛውን ትዕዛዝ ነው ያከበረው?
የሰንበትን ቀን አክብር የሚለውን
''የባልንጀራህን ቤት አትመኝ'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘፀ 20:13 ለ. ዘፀ 20:17 ሐ. ዘፀ 20:6
ለ. ዘፀ 20:17
''ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ'' የሚለው ትዕዛዝ በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?
ሀ. ዘሌ 19:18 ለ. ዘሌ 19:1 ሐ. ዘሌ 19:10
ሀ. ዘሌ 19:18
''አባትህን እና እናትህን አክብር'' የሚለው ስንተኛው ትዕዛዝ ነው?
ሀ. 4ኛው ለ. 3ኛው ሐ. 5ኛው
ሀ. 4ኛው
ሎአና ከአስተማሪዋ የወሰደችውን እርሳስ ተጠቅማ ስትጨርስ መለሰችለት። ስንተኛውን ትዕዛዝ አከበረች?
ሀ. 7ኛው ለ. 6ኛው ሐ. 5ኛው
ሀ. 7ኛው
እልልታ የራሷን መጫወቻ እንጂ የሌላ ሰው መጫወቻ አትመኝም።
የትኛውን ትዕዛዝ ነው ያከበረችው?
የባልንጀራህን ቤት አትመኝ የሚለውን