Which judge made a rash vow to sacrifice whatever first came out of his house, leading to the sacrifice of his only daughter?
ወደ ቤቱ ሲመለስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበለውን ለማሥዋዕትነት የተሳለና ብቸኛ ልጁን መሥዋዕት ያደረገው መስፍን ማን ነው?
Who is Jephthah? / ዮፍታሔ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: Judges 11:30–35 / መጽሐፈ መሳፍንት 11:30–35
At whose pool in Jerusalem did Jesus heal a man who had been paralyzed for 38 years?
ኢየሱስ ለ38 ዓመታት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረው ሰው የፈወሰው በኢየሩሳሌም በሚገኘው በየትኛው መጠመቂያ አጠገብ ነው?
What is Bethesda? / ቤተሳይዳ (ቤተ ሔስዳ)? Reference / ምንጭ: John 5:2–9 / የዮሐንስ ወንጌል 5:2–9
Which Syrian army commander was healed of leprosy after dipping seven times in the Jordan River?
በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ በመጠመቅ ከለምጽ የተፈወሰው የሶርያ ሠራዊት አለቃ ማን ነው?
Who is Naaman? / ንዕማን ማን ነው?
Reference / ምንጭ: 2 Kings 5:14 / 2ኛ ነገሥት 5:14
In which epistle does Paul write that "the root of all kinds of evil is the love of money"?
ጳውሎስ "የክፋት ሁሉ ሥር ገንዘብን መውደድ ነው" ብሎ የጻፈው በየትኛው መልእክቱ ውስጥ ነው?
What is 1 Timothy? / 1ኛ ጢሞቴዎስ?
Reference / ምንጭ: 1 Timothy 6:10 / 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:10
In what garden was Jesus betrayed by Judas with a kiss?
ኢየሱስ በይሁዳ በመሳም አሳልፎ የተሰጠበት አትክልት ቦታ ስም ማን ይባላል?
What is Gethsemane? / ጌቴሴማኔ?
Reference / ምንጭ: Matthew 26:36 / የሜቴዎስ ወንጌል 26:36
What pieces of news did Eli receive right before he fell off his chair and died?
ዔሊ ከወንበሩ ወድቆ ከመሞቱ በፊት የተነገርው መጥፎ ዜናዎች ምን ነበሩ?
His two sons (Hophni and Phinehas) died, and the Ark of God was captured?
ሁለቱ ልጆቹ (አፍኒና ፊንሐስ) መሞታቸው እና የእግዚአብሔር ታቦት መማረኩ?
Reference / ምንጭ: 1 Samuel 4:17–18 / 1ኛ ሳሙኤል 4:17–18
Whose shadow falling upon the sick resulted in their healing as described in the Book of Acts?
በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ጥላው በሕመምተኞች ላይ ሲያርፍ ይፈወሱ የነበረው የማን ነው?
Who is Peter? / ጴጥሮስ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: Acts 5:15 / የሐዋርያት ሥራ 5:15
With only how many men did Gideon defeat the Midianite army using torches, jars, and trumpets? / ጌዴዎን በችቦ፣ በማሰሮና በከበሮ የ ምድያማውያንን ሠራዊት ያሸነፈው በስንት ሰዎች ነበር?
What is 300 men? / 300 ሰዎች?
Reference / ምንጭ: Judges 7:7 / መጽሐፈ መሳፍንት 7:7
Who was the Roman centurion in Caesarea whose entire household converted after an angel directed him to Peter?
መልአክ ወደ ጴጥሮስ እንዲሄድ ከነገረው በኋላ ቤተሰቡ በሙሉ ያመነው የሮም መቶ አለቃ ማን ነው?
Who is Cornelius? / ቆርኔሌዎስ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: Acts 10:1–2 / የሐዋርያት ሥራ 10:1–2
Where did Elijah challenge and defeat the 450 prophets of Baal?
ኤልያስ 450 የባኦል ነቢያትን የተፈታተነበትና ያሸነፈበት ቦታ የት ነው?
What is Mount Carmel? / ቀርሜሎስ ተራራ?
Reference / ምንጭ: 1 Kings 18:19 / 1ኛ ነገሥት 18:19
What city did David make his capital and rule over Judah from for seven and a half years before capturing Jerusalem?
ዳዊት ኢየሩሳሌምን ከመቆጣጠሩ በፊት ለሰባት ዓመት ተኩል በይሁዳ ላይ የነገሠበትና መዲናው ያደረጋት ከተማ የትኛዋ ናት?
What is Hebron? / ኬብሮን?
Reference / ምንጭ: 2 Samuel 2:1, 11 / 2ኛ ሳሙኤል 2:1, 11
What specific miracle occurred when Jesus paid the temple tax for himself and Peter in Matthew 17?
በወንጌላዊው ማቴዎስ ምዕራፍ 17 ላይ ኢየሱስ የቤተ መቅደስ ግብር ለራሱና ለጴጥሮስ ሲከፍል የተደረገው ድንቅ ተአምር ምን ነበር?
What is finding a coin (a stater) inside the mouth of the first fish Peter caught?
ጴጥሮስ በመጀመሪያ ባወጣው ዓሣ አፍ ውስጥ ሳንቲም (እስታቴር) ማግኘት?
Reference / ምንጭ: Matthew 17:27 / የሜቴዎስ ወንጌል 17:27
Which king of Judah had his life extended by 15 years after praying to God, and had the shadow on the sundial move backward 10 steps as a sign?
ወደ እግዚአብሔር በመጸለዩ 15 ዓመት ተጨማሪ ዕድሜ የተሰጠውና በፀሐይ ሰዓት ላይ ያለው ጥላ 10 ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ ምልክት የተሰጠው የይሁዳ ንጉሥ ማን ነው?
Who is King Hezekiah? / ንጉሥ ሕዝቅያስ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: 2 Kings 20:5–11 / 2ኛ ነገሥት 20:5–11
Which companion of Paul deserted him during his second imprisonment in Rome because he "loved this present world"?
"ይህን ዓለም ወዶ" በሮሜ ሁለተኛ እስሩ ወቅት ጳውሎስን ትቶ የሄደው የጳውሎስ አጋር ማን ነው?
Who is Demas? / ዴማስ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: 2 Timothy 4:10 / 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:10
What specific city’s gate was Jesus approaching when he raised a widow’s only son from the dead?
ኢየሱስ የመበለቲቱን አንድ ልጅ ከሞት ያስነሳው ወደ የትኛዋ ከተማ በር ሲቀርብ ነበር?
What is Nain? / ናይን?
Reference / ምንጭ: Luke 7:11–12 / የሉቃስ ወንጌል 7:11–12
Who was the army commander of King Saul who later reconciled with David before being killed by Joab?
የሳኦል የሠራዊት አለቃ የነበረውና በኋላ ከዳዊት ጋር ቢታረቅም በኢዮአብ የተገደለው ማን ነው?
Who is Abner? / አበኔር ማን ነው?
Reference / ምንጭ: 2 Samuel 3:27 / 2ኛ ሳሙኤል 3:27
During the Exodus, what did Moses throw into the bitter waters of Marah to make them sweet and drinkable?
በጉዞ ወቅት ሙሴ የማራን መራራ ውኃ ለማጣፈጥና የሚጠጣ ለማድረግ ወደ ውኃው ውስጥ የጣለው ምን ነበር?
What is a piece of wood (a tree)? / እንጨት (ዛፍ)?
Reference / ምንጭ: Exodus 15:25 / ዘጸአት 15:25
Which king of Israel built Samaria as his capital city and was the father of King Ahab?
ሰማርያ መዲናው አድርጎ የገነባውና የንጉሥ አክዓብ አባት የነበረው የእስራኤል ንጉሥ ማን ነው?
Who is Omri? / ኦምሪ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: 1 Kings 16:23–24 / 1ኛ ነገሥት 16:23–24
In Acts 16, which disciple joined Paul and Silas on their missionary journey in Lystra, whose mother was Jewish and father was Greek? / በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 16 ላይ በልስጥራ ጳውሎስንና ሲላስን የተቀላቀለው፣ እናቱ አይሁዳዊት አባቱ ግን ግሪክ የነበረው ደቀ መዝሙር ማን ነው?
Who is Timothy? / ጢሞቴዎስ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: Acts 16:1–3 / የሐዋርያት ሥራ 16:1–3
What island was Paul shipwrecked on while traveling as a prisoner to Rome?
ጳውሎስ እስረኛ ሆኖ ወደ ሮሜ ሲጓዝ መርከቡ የተሰበረባት ደሴት ስም ማን ይባላል?
What is Malta? / መላጥያ ደሴት?
Reference / ምንጭ: Acts 28:1 / የሐዋርያት ሥራ 28:1
Which high priest discovered the Book of the Law in the temple during King Josiah's reign?
በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሕጉን መጽሐፍ ያገኘው ሊቀ ካህን ማን ነው?
Who are Hilkiah
ሊቀ ካህኑ ኬልቂያስ
Reference / ምንጭ: 2 Kings 22:8, 14 / 2ኛ ነገሥት 22:8, 14
Which king of Judah was struck with leprosy in the temple after pridefully burning incense at the altar, an act reserved only for priests?
በካህናት ላይ ብቻ የተፈቀደውን ዕጣን በቤተ መቅደስ ስለ ማጠናቱ በትዕቢቱ ምክንያት በለምፅ የተመታው የይሁዳ ንጉሥ ማን ነው?
Who is King Uzziah ? / ንጉሥ ዖዝያን ማን ነው?
Reference / ምንጭ: 2 Chronicles 26:16–21 / 2ኛ ዜና መዋዕል 26:16–21
Which king had his eyes put out by the king of Babylon after seeing his sons killed before him at Riblah?
በሪብላ ዐይኑ እያየ የገዛ ልጆቹን ከገደሉበት በኋላ በባቢሎን ንጉሥ ዓይኖቹ የወጡበት ንጉሥ ማን ነው?
Who is Zedekiah? / ሴዴቅያስ ማን ነው?
Reference / ምንጭ: 2 Kings 25:6–7 / 2ኛ ነገሥት 25:6–7
Which early Christian woman is described in Romans 16 as a deacon/deaconess of the church in Cenchreae?
በሮሜ 16 ላይ የክንክሬኦስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ዲያቆን ተብላ የተገለጸችው የመጀመሪያዋ ክርስቲያን ሴት ማን ናት?
Who is Phoebe? / ፌቤን ማን ናት?
Reference / ምንጭ: Romans 16:1 / ወደ ሮሜ ሰዎች 16:1
In Ezekiel 27, which famous island city-state is described as the trading hub of the ancient world whose sailors, merchants, and wealth would undergo a total downfall?
በሕዝቅኤል ምዕራፍ 27 ላይ የመርከበኞች፣ የነጋዴዎችና የታላቅ ሀብት ማዕከል እንደነበረችና በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ እንደምትወድቅ የተነገረላት ታዋቂዋ የደሴት ከተማ የትኛዋ ናት?
What is Tyre? / ጢሮስ?
Reference / ምንጭ: Ezekiel 27:3, 26–27 / ትንቢተ ሕዝቅኤል 27:3, 26–27