ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው የት ነው?
Where was our Lord Jesus Christ baptized?
ጌታችን የተጠመቀው በዮርዳኖስ ወንዝ ነዉ
Our Lord was baptized in the Jordan River.
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በማን እጅ ነው?
By whose hands was our Lord Jesus Christ baptized?
የተጠመቀው በቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እጅ ነው
He was baptized by Saint John the Baptist.
ጌታችን ለምን ተጠመቀ?
Why was our Lord baptized?
ለእኛ አርአያ ለመሆንና የሥላሴን ምስጢር ለመግለጥ
To be an example for us and to reveal the mystery of the Trinity
ለጌታችን ስግደትና ስጦታ ያቀረቡት ሰዎች ማን በመባል ይይታወቃሉ?
What do we call those people who worshipped and offered gifts to our Lord?
ሰብአ ሰገል (ከሰማያዊ ኮከብ መሪነት ጋር የመጡ የጥበብ ሰዎች)።
The Wise Men (wise men who came with the guidance of a celestial star).
ጌታ በተወለደ ጊዜ ሕፃናትን ያስፈጀው ንጉሥ ማን ይባላል?
Who was the king who devoured the children when the Lord was born?
ንጉሥ ሄሮድስ።
King Herod.
የጥምቀት በዓል በቤተክርስቲያን ቀኖና መሠረት ስንት ቀናት ይከበራል?
How many days is the feast of Baptism celebrated according to church canon?
ለ3 ቀናት ፣ከጥር 11-13
For 3 days January 11-13.
ጌታችን የተጠመቀው በስንት ዓመቱ ነው?
At what age was our Lord baptized?
በ30 ዓመቱ ነበር (ሉቃስ 3፡23)
He was 30 years old (Luke 3:23).
አብ በደመና ሆኖ ምን አለ?
What did the Father say while in the cloud?
"በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው" አለ።
"This is my beloved son, in whom I am well pleased," he said.
ሄሮድስ ሕፃናትን እንዲገደሉ ያዘዘው ከስንት ዓመት በታች ያሉትን ነው?
Herod ordered the killing of children under what age?
ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑትን።
Those aged two years and under.
ሰብአ ሰገል ያቀረቡለት ስጦታዎች ምን ምን ናቸው?
What are the gifts that the wise men brought him?
ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ።
Gold, frankincense, and myrrh.
ዮርዳኖስ ወደ ኋላ የተመለሰው ለምንድነው?
Why did the Jordan river turn back?
የፈጣሪውን ግርማ ስላየ (መዝ 113፡3)።
Because he saw the glory of the Creator (Psalm 113:3).
ጌታችን ከተጠመቀ በኋላ ያደረገው የመጀመሪያው ተአምር ምንድነው?
What was the first miracle our Lord performed after his baptism?
ውኃውን ወደ ወይን መለወጥ። (ዮሐንስ 2፡1-11)
Turning water into wine (John 2:1-11)
ጌታችን ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያው ተአምር ያደረገው የት ነው?
Where was the first place where our Lord Jesus performed the first miracle after his baptism?
በቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ ውኃውን ወደ ወይን መለወጥ። (ዮሐንስ 2፡1-11)
Turning water into wine at the wedding in Cana of Galilee (John 2:1-11)
መላእክት የጌታን ልደት መጀመሪያ ያበሰሩት ለማን ነው?
To whom did the angels first announce the birth of the Lord?
በሜዳ ለነበሩ እረኞች።
To the shepherds who were in the field.
"ኢየሱስ" ማለት ምን ማለት ነው?
What does "Jesus" mean?
መድኃኒት ወይም አዳኝ ማለት ነው።
It means medicine or savior.
በጥምቀቱ ወቅት መንፈስ ቅዱስ በምን አምሳል ወረደ?
In what form did the Holy Spirit descend during baptism?
በርግብ አምሳል።
In the form of a dove.
በጥምቀት የምናገኘው ጸጋ ምንድነው?
What is the grace we receive in baptism?
ከእግዚአብሔር የመወለድ የልጅነት ጸጋ።
The grace of childhood, born of God.
ጌታችን ለመጠመቅ ሲመጣ ዮሐንስ መጥምቅ መጀመሪያ ምን አለ?
When our Lord came to be baptized, what did John the Baptist say first?
"እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?" (ማቴዎስ 3፡14)።
“I need to be baptized by you, and do you come to me?” (Matthew 3:14).
የሰብአ ሰገል ስጦታ "ከርቤ" ምንን ያመለክታል?
What does the gift from the wise men, "myrrh," symbolize?
ለጌታችን መከራ መቀበሉንና ሞቱን።
The suffering and death of our Lord.
የሰብአ ሰገል ስጦታ "ወርቅ" ምንን ያመለክታል?
What does the gift of the wise men, "gold," symbolize?
ለጌታችን ንጉሥነቱን (መንግሥቱን)።
Our Lord's power and kingdom.
ጌታችን ለምን ተጠመቀ? (እርሱ ንጹሕና ኃጢአት የሌለበት ሆኖ ሳለ)
ዋና ዋና ምክንያቶቹ)
Why was our Lord baptized? (While He was pure and sinless. The main reasons)
• ለእኛ አርአያ (ምሳሌ) ለመሆን።
• የሥላሴን ምስጢር ለመግለጥ (አብ በደመና፣ ወልድ በሥጋ፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል)።
• የአዳምን የዕዳ ደብዳቤ ለመደምሰስ።
• ውኃን ለመቀደስና የጥምቀትን ሥርዓት ለመመሥረት።
• To be an example for us.
• To reveal the mystery of the Trinity (Father in the cloud, Son in the flesh, Holy Spirit in the form of a dove).
• To erase Adam's debt.
• To sanctify water and establish the ordinance of baptism.
ዮርዳኖስ ወደ ኋላ የተመለሰው ለምንድነው?
Why did Jordan turn back?
የፈጣሪውን ግርማ ስላየ (መዝ 113፡3)።
Because it saw the glory of its Creator (Ps. 113:3).
ዮሐንስ መጥምቅ ጌታን ሲያይ ምን ብሎ መሰከረ?
What did John the Baptist testify when he saw the Lord?
"የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!" (ዮሐንስ 1፡29)።
"The Lamb of God, who takes away the sin of the world!" (John 1:29).
የሰብአ ሰገል ስጦታ "ዕጣን" ምንን ያመለክታል?
What does the gift from the wise men, "incense," represent?
ለጌታችን አምላክነቱን (ክህነቱን)።
His Godship (priesthood) to our Lord.
ሕፃኑን ጌታ በቤተ መቅደስ የታቀፈው አረጋዊ ማን ነው?
Who is the old man who held the infant Lord in the temple?
ቅዱስ ስምዖን።
Saint Simon.