ፈጥሯቸዋልና እነዲገለጽ ክብሩ
ሂድ ንገሩ አውሩ ለዓለም ተነሥቷል በዚህ የለም
መድኃኒዓለም ሞት የማይችለው የበረታ
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ ነቢያት በሙሉ ነቢያት በሙሉ
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ ይወርዳል እያሉ ይወርዳል እያሉ
የአለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ
እንዘ ስውር እምኔነ
ይእዜሰ ክሱተ ኮነ
ያላንተ ጌታ ደስታ መች አለ ያላንተ አምላኬ ሕይወት መች አለ
ስምህን ጠርቶ የተማፀነ ከእሳትም ወጣ ከሞትም ዳነ
ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ የሚያንጸባርቅ፣
የአምላክ እና የሰው ልጆች እውነተኛ እርቅ፣
አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት
ባንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት
መጣ ቃል ከደመና እንዲህ የሚል
የምወደው የማፈቅረው ልዼ ይህ ነው
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ኹሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላቸው
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግሥቱ መርጧታልና
ማደርያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
መላእክቱ ነጭ ለብሰው ምስራቹን አበሰሩ
ተነስቷል ኢየሱስ ብለው ለዓለም እንዲናገሩ
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም በቤተልሔም ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ/፪/ በቤተልሔም
ግነዮ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር
እስመ ለዓለም ምህረቱ እስመ ለዓለም
ሐናና ኢያቄም በጸሎት ሲተጉ
በፈጣርያቸው ፊት መልካሙን ቢያደርጉ
በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ
አለሁ እስከ ዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ
ክርስቶስ ተነሣ ከሙታን በታላቅ ኃይል በታላቅ ሥልጣን
ሰይጣንን አስሮ/፪/ ኧኸ ኧኸ ነፃ አወጣን አዳምን
ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና
ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና
ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ
በሄኖን በቅሩበ ሳሌም
ታውቋት ስላለችው…በማየ ቀና
ወይንኪ አልቦሙ…በማየ ቃና
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ከምንም በፉት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ ምስጋና ይገባል ከጠዋት እስከ ማታ
የምሥራች እንበል/፪/ እናመስግን ጌታን
በመስቀል ላይ ውሎ ከኃጢአት ላነፃን
መንጋውን በሌሊት ሲጠብቁ እረኞች
ከሰማይም ሰሙ ታላቅ የምሥራች
ጌታችን ሲጠመቅ ባህር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
በቤተ ክርስቲያን ጥላ ተከልለው
ተክሊል አድርገዋል ሙሽሪት ሙሽራ
አይቼ የእዽህን ታምራት
ሰምቼ የቃልህን ትምህርት
ሆኛለው ምስክር ለአዳኝንተህ
ሥጋን ተዋሕደህ ለኛ መገለጥህ