"The nakedness of your father or the nakedness of your mother you shall not uncover. She is your mother; you shall not uncover her nakedness. The nakedness of your father’s wife you shall not uncover; it is your father’s nakedness. The nakedness of your sister, the daughter of your father, or the daughter of your mother, whether born at home or elsewhere, their nakedness you shall not uncover."
" ‘ከእናትህ ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም አባትህን አታዋርድ፤ እናትህ ናት፤ ከእርሷ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ። “ ‘ከአባትህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አባትህን ያዋርዳል። “ ‘ከእኅትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፣ ከአባትህ ወይም ከእናትህ ሴት ልጅ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።'"
Leviticus 18:7-9 | New King James Version
ዘሌዋውያን 18፡7-9 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
"And they were not able to resist the wisdom and the Spirit by which he spoke. Then they secretly induced men to say, 'We have heard him speak blasphemous words against Moses and God.' And they stirred up the people, the elders, and the scribes; and they came upon him, seized him, and brought him to the council. They also set up false witnesses who said, 'This man does not cease to speak blasphemous words against this holy place and the law; ...'"
"ነገር ግን ይቃወሙት ዘንድ አልቻሉም፤ በጥበብና በመንፈስ ቅዱስ ይከራከራቸው ነበርና። ከዚህም በኋላ 'ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል' የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አስነሡበት፤ ሕዝቡን፥ ሽማግሌዎችንና ጸሓፊዎችንም አነሳሡአቸው፤ ከበውም እየጐተቱ ወደ ሸንጎ አቀረቡት። የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ እነርሱም እንዲህ አሉ፥ 'ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስ ላይና በኦሪት ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤'"
The Acts of The Apostles 6:10-13 | New King James Version
የሐዋርያት ሥራ 6፡10-13 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
Who beat his donkey and kept going without understanding after the Angel of The Lord stopped his donkey thrice?
Prophet Balaam
#1
The Burnt Offering
#1
The Apostle
"Then I returned and considered all the oppression that is done under the sun: And look! The tears of the oppressed, But they have no comforter— On the side of their oppressors there is power, But they have no comforter. Therefore I praised the dead who were already dead, More than the living who are still alive. Yet, better than both is he who has never existed, Who has not seen the evil work that is done under the sun."
"እንደ ገና ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ አስተዋልሁም፤ የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ ኀይል በሚገፏቸው ሰዎች እጅ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም። እኔም የቀድሞ ሙታን፣ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ፣ ደስተኞች እንደ ሆኑ ተናገርሁ። ነገር ግን ከሁለቱም ይልቅ፣ ገና ያልተወለደው፣ ከፀሓይ በታች የሚደረገውንም፣ ክፋት ያላየው ይሻላል።"
Ecclesiastes 4:1-3 | New King James Version
መክብብ 4፡1-3 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
"For this reason I bow my knees to the Father of our Lord Jesus Christ, from whom the whole family in heaven and earth is named, that He would grant you, according to the riches of His glory, to be strengthened with might through His Spirit in the inner man, that Christ may dwell in your hearts through faith; that you, being rooted and grounded in love, may be able to comprehend with all the saints what is the width and length and depth and height— to know the love of Christ which passes knowledge; that you may be filled with all the fullness of God."
"በዚህም ምክንያት በአብ ፊት እንበረከካለሁ፤ ከእርሱም በሰማይና በምድር ያለ ቤተ ሰብ ሁሉ ስያሜ ያገኛል። በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤ ይኸውም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲያድር ነው። ደግሞም ሥር ሰድዳችሁ፣ በፍቅር ታንጻችሁ፣ የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ፣ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር የመገንዘብ ኀይልን እንድታገኙ ነው። እስከ እግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ፣ ከመታወቅ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ታውቁም ዘንድ ነው።"
Paul's Epistle to The Ephesians 3:14-19 | New King James Version
ኤፌሶን 3፡14-19 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
To whom did Apostle Paul say, "'Preach the word; be instant in season, out of season; reprove, rebuke, exhort with all longsuffering and doctrine.'"
Timothy
#2
The Sin Offering
#2
The Prophet
“At that time Michael shall stand up, The great prince who stands watch over the sons of your people; And there shall be a time of trouble, Such as never was since there was a nation, Even to that time. And at that time your people shall be delivered, Every one who is found written in the book. And many of those who sleep in the dust of the earth shall awake, Some to everlasting life, Some to shame and everlasting contempt. Those who are wise shall shine Like the brightness of the firmament, And those who turn many to righteousness Like the stars forever and ever."
“በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ። በምድር ዐፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጕስቍልና ይነሣሉ። ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።"
Daniel 12:1-3 | New King James Version
ዳንኤል 12፡1-3 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
"For even when we were with you, we commanded you this: If anyone will not work, neither shall he eat. For we hear that there are some who walk among you in a disorderly manner, not working at all, but are busybodies. Now those who are such we command and exhort through our Lord Jesus Christ that they work in quietness and eat their own bread. But as for you, brethren, do not grow weary in doing good. And if anyone does not obey our word in this epistle, note that person and do not keep company with him, that he may be ashamed. Yes do not count him as an enemy, but admonish him as a brother."
"ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ፣ 'ሊሠራ የማይወድድ አይብላ' ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና። ከእናንተ አንዳንዶች ሥራ ፈቶች እንደ ሆኑ ሰምተናል፤ እነርሱም ያለ ሥራ እየዞሩ በሰው ጕዳይ ጣልቃ የሚገቡ ናቸው። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተግተው ሥራቸውን እንዲሠሩና እንጀራቸውን እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም። እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፤ መልካም ሥራን ከመሥራት ከቶ አትታክቱ። በዚህ መልእክት ላይ ላለው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ እንደዚህ ያለውን ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት፤ በሥራውም እንዲያፍር ከእርሱ ጋር አትተባበሩ። ሆኖም እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።"
Paul's Second Epistle to The Thessalonians 3:10-15 | New King James Version
2 ተሰሎንቄ 3፡10-15 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
"'Certain of the Jews banded together, and bound themselves under a curse, saying that they would neither eat nor drink till they had killed ____.'"
Apostle Paul
#3
The Trespass Offering
#3
The Evangelist
"'I went down to the moorings of the mountains; The earth with its bars closed behind me forever; Yet You have brought up my life from the pit, O Lord, my God. “When my soul fainted within me, I remembered the Lord; And my prayer went up to You, Into Your holy temple. “Those who regard worthless idols Forsake their own Mercy. But I will sacrifice to You With the voice of thanksgiving; I will pay what I have vowed. Salvation is of the Lord.'"
"'ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ግን ሕይወቴን ከጕድጓድ አወጣህ። “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች። “ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፣ ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ። እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።'"
Jonah 2:6-9 | New King James Version
ዮናስ 2፡6-9 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
"But as for you, speak the things which are proper for sound doctrine: that the older men be sober, reverent, temperate, sound in faith, in love, in patience; the older women likewise, that they be reverent in behavior, not slanderers, not given to much wine, teachers of good things— that they admonish the young women to love their husbands, to love their children, to be discreet, chaste, homemakers, good, obedient to their own husbands, that the word of God may not be blasphemed."
"አንተ ግን ከትክክለኛው ትምህርት ጋር ተስማሚ የሆነውን አስተምር። አረጋውያን ጭምቶች፣ የተከበሩ፣ ራሳቸውን የሚገዙና በእምነት፣ በፍቅርና በትዕግሥት ጤናማነት ያላቸው እንዲሆኑ ምከራቸው። እንዲሁም አሮጊቶች በአኗኗራቸው የተከበሩ እንዲሆኑ፣ በጎ የሆነውን የሚያስተምሩ እንጂ የሰው ስም የሚያጠፉ ወይም በወይን ጠጅ ሱስ የተጠመዱ እንዳይሆኑ አስተምራቸው። እንዲህ ከሆኑ፣ ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወድዱ ማስተማር ይችላሉ፤ የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።"
Paul's Epistle to Titus 2:1-5 | New King James Version
ቲቶ 2፡1-5 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
Who was the wife of Moses?
Zipporah
#4
The Grain Offering
#4
The Pastor
"God came from Teman, The Holy One from Mount Paran. ... His glory covered the heavens, And the earth was full of His praise. His brightness was like the light; He had rays flashing from His hand, And there His power was hidden. Before Him went pestilence, And fever followed at His feet. He stood and measured the earth; He looked and startled the nations. And the everlasting mountains were scattered, The perpetual hills bowed. His ways are everlasting."
"እግዚአብሔር ከቴማን፣ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። ... ክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ ውዳሴውም ምድርን ሞላ። ጸዳሉ እንደ ፀሓይ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጣ፤ ኀይሉም በዚያ ተሰውሯል። መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው። ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤ የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤ የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤ መንገዱ ዘላለማዊ ነው።"
Habakkuk 3:3-6 | New King James Version
ዕንባቆም 3፡3-6 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
"Beloved, let us love one another, for love is of God; and everyone who loves is born of God and knows God. He who does not love does not know God, for God is love. In this the love of God was manifested toward us, that God has sent His only begotten Son into the world, that we might live through Him. In this is love, not that we loved God, but that He loved us and sent His Son to be the propitiation for our sins. Beloved, if God so loved us, we also ought to love one another."
"ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። የማይወድድ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፤ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በእርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ። ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው። ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፣ እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል።"
I John 4:7-11 | New King James Version
1 የዮሐንስ መልእክት 4፡7-11 | አዲሱ መደበኛ ትርጉም
Who was the wife of Joseph?
Asenath
#5
The Peace Offering
#5
The Teacher