በገና ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በማን አማካኝነት ነው?
ሀ. በአጼ ኃይለሥላሴ
ለ. በአጼ ቴዎድሮስ
ሐ. በቀዳማዊ ምኒሊክ
ሐ. በቀዳማዊ ምኒሊክ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመሰለው የበገና አካል ክፍል ''ጌጥ'' ይባላል።
ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
ለ. ሐሰት
በመንፈስ ቅዱስ የሚመሰለው መቃኛ ነው
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልቶች የሚባሉት ስንት ናቸው? ስማቸው ማን ማን ይባላል?
3(ሶስት) ናቸው።
እነሱም ግዕዝ፣ ዕዝል እና አራራይ
የአንቺ ሆዬ ቅኝት ድምጽ በ''C" ሜጀር ሲነሳ
ሀ. C D F G A C
ለ. C D F F# G C
ሐ.C C# F F# A C
መ.C D E G A C
ሐ. C C# F F# A C
በገና ከመደርደራችን በፊት ማደረግ ካሉብን ነገሮች ሁለቱን ጥቀሱ
1 አለባበሳችንን ማስተካከል
2 ጸሎት ማድረግ
3 አቀማመጣችንን ማስተካከል
4 በገናችንን በአግባቡ መያዝ
ከሚከተሉት ውስጥ የበገና ትርጉም ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ነዘረ
ለ. መታ
ሐ. ደረደረ
መ. መልሱ የለም
መ. መልሱ የለም
__________ በተጋድሎ ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ይመሰላል።
እንዚራ
pentatonic የምንለው ባለ 7 ድምጽ ነው
ሀ. እውነት
ለ. ሐሰት
ለ. ሐሰት
የአንቺ ሆዬ ቅኝት የድምጽ ርቀት 1/2፣ 2፣ 1/2፣ 11/2፣ 11/2 ነው
ሀ. እውነት
ለ. ሐሰት
ሀ. እውነት
መዝሙር ለማን ለማን ሊቀርብ ይችላል?
ሀ. ለእግዚአብሔር ሐ. ለቅዱሳን መካናት
ለ. ለቅዱሳን መላዕክት እና ሰማዕታት መ. ለሰንበት
ሠ. ሁሉም መልስ ነው።
ሠ. ሁሉም መልስ ነው።
ከበገና ጥቅሞች የሚመደበው የቱ ነው?
ሀ. ምስጋና ለማቅረብ መ. ትንቢትን ለመናገር
ለ. እርኩስ መንፈስን ለማራቅ ሠ. ሁሉም መልስ ነው
ሐ. ታቦትን ለማጀብ
ሠ. ሁሉም መልስ ነው
በሐዲስ ኪዳን የሚመሰለው የበገና አካል ክፍል የቱ ነው?
የግራ ምሰሶ
በድምጾች መካከል ያለው የድምጽ ርቀት መለኪያ ምን ተብሎ ይጠራል?
ቶን (Tone)
ምሳሌ፡ C D በእነዚህ ድምጽ መካከል ያለው ርቀት 1T (አንድ ሙሉ ድምጽ)
C C# በእነዚህ ድምጽ መካከል ያለው ርቀት 1/2T (ግማሽ ድምጽ)
1፣ 1፣ 11/2፣ 1፣ 11/2 ይሄ የየትኛው የቅኝት የድምጽ ርቀት (ቀመር) ነው?
ሀ. የሰላምታ
ለ. የትዝታ
ሐ. የአንቺ ሄዬ
ለ. የትዝታ
ከሚከተሉት ውስጥ የዜማ መሳሪያ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከበሮ መ. በገና
ለ. መቋሚያ ሠ. መልሱ የለም
ሐ. ዋሽንት
ሠ. መልሱ የለም
የተጠቀሱት ሁሉም የዜማ መሳሪያ ናቸው።
በገና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሶ የምናገኘው በየትኛው ክፍል ነው?
ሀ. በብሉይ ኪዳን
ለ. በሐዲስ ኪዳን
ሐ. በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን
መ. በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጠቀሰም
ሐ. በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን
በገና በሁለት መልኩ ልንደረድር እንችላለን። አንዱ በእጃችን (በጣታችንን) ሲሆን ሁለተኛውን በምን ልንደረድር እንችላለን? ምሳሌነቱስ ምንድነው?
በድህንጻ
ምሳሌነቱም የክርስቶስ ምሳሌ ነው
አንድን ድምጽ በግማሽ ለመቀነስ የሚያስችለን #(ሻርፕ) ይባላል።
ሀ. እውነት
ለ. ሐሰት
ለ. ሐሰት
በግማሽ ለመቀነስ የሚያስችለን b(flat) ተብሎ ይጠራል
በግማሽ ደግሞ ለመጭመር የሚያስችለን #(ሻርፕ) ይባላል
ሰላምታ ቅኝት ከተፈጥሮአዊው ቅኝት(Basic Sounds) ስንተኛውን እና ስንተኛውን ስናወጣ ነው የምናገኘው?
3ኛውን እና 7ኛውን
ሰባቱ ድምጾች - C D E F G A B C
3ኛው E
7ኛው B
ሲወጣ - C D F G A C
ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ የተጀመረው በቅዱስ ያሬድ ጊዜ ነው?
ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
ለ. ሐሰት
እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ በፊት ባህሪው ባህሪውን ያመሰግን እንደነበር በዮሐ፡- 17 - 5
የሰው ልጅ በገናን መጠቀም ከጀመረ ለስንት ዓመታት ይሆናል?
ሀ. ከ5816 ዓመት በላይ
ለ. ከ300 ዓመት በላይ
ሐ. ከ1900 ዓመት በላይ
መ. ከ20 ዓመት በላይ
ሀ. ከ5816 ዓመት
በገናችን ላይ ከድምጽ ሳጥኑ ጀርባ ያለው ቅርጽ የምን ምልክት ነው? ምሳሌነቱስ ምንድነው?
ምልክቱ ''የመስቀል ምልክት ነው"
ምሳሌነቱ ዳዊት ከሳኦል ጦር የዳነበት
የቤተክርስቲያን የዜማ መሳሪያዎች አከፋፈል - በገና አውታር ካላቸው መሳሪያዎች ጋር የሚመደብ ነው
ሀ እውነት
ለ ሐሰት
ሀ. እውነት
የዜማ መሳሪያዎች በ 3 ይከፈላሉ
1. አውታር ያላቸው፦ በገና፣ መሰንቆ
2. በእስትንፋስ የሚነፉ ፦ ዋሽንት፣ መለከት
3. እርስ በርስ በማማታት የሚሰሩ፦ ከበሮ እና ጸናጽል
የትዝታ ቅኝት ከ''F'' ሜጀር ስንነሳ የምናገኘው ድምጽ
ሀ. F G A C Db F
ለ. F G A# C D F
ሐ. F G A C D F
ሐ. F G A C D F
በገና ከእንስሳት እና ከእጽዋት ተዋጽኦ ማለትም ከእንስሳት፦ ከበግ (ከበሬ) አንጀት፣ ከቆዳ፣ ከቀንድ እንዲሁም ከእጽዋት ደግሞ ከዋንዛ፣ ዝግባ እንጨቶች የሚሰራ ነው። ከእንስሳት ተዋጽኦ እና ከእጽዋት የሚሰሩት የበገና አካል ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?
ከእጽዋት፦
ቀንበር(ጋድም)፣ የድምጽ ሳጥን፣ በርኩማ፣ መቃኛ እና መወጠሪያ
ከእንስሳት ተዋጽኦ፦ አውታር፣ እንዚራ፣ የድምጽ ሳጥኑ ልብስ፣
የመወጠሪያ ማሰሪያ፣ ድህንጻ