ለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን
ሀ)ሮሜ 8፡1
ለ) ዮሐ 1፡1
ሐ)1 ዮሐ 1፡1
መ)ዕብ 1፡1
ሐ) 1 ዮሐ 1፡1
ኑኃሚን ከሩት ጋር ወደ እስራኤል ስትመለስ የሄደችው ወደ የትኛው ከተማ ነው?
ሀ) ሞአብ
ለ) ኢየሩሳሌም
ሐ)ቤተልሔም
መ)ቂሳሪያ
ሐ)ቤተልሔም
የዮሃንስ ራዕይ ስንት ምእራፎች አሉት?
22
ያይሃል ኢየሱስ ያይሃል የሚል መዝሙር አለኝ፤ እኔ ማነኝ?
ተስፋዬ ጋቢሶ
እግዚአብሔር የምድሪቱን ከእርሱ ርቃ በኃጢያት መሆኗን ለማሳየት ጋለሞታ እንዲያገባ የነገረው ነብይ ማነው?
ሀ)አሞጽ
ለ)ሆሴዕ
ሐ)ኢዮኤል
መ)ሚኪያስ
ለ)ሆሴዕ
ሆሴ 1፡2-9
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል የሚለው ጥቅስ የት ይገኛል?
ሀ) ቆላ 3፡23
ለ) ገላ 3፡13
ሐ) ሮሜ 3፡23
መ) ፊል 3፡13
ሐ) ሮሜ 3፡23
የኤርሚያስን ትንቢት እንዲጽፍ የተነገረው ማን ነው?
ሀ) ዕዝራ
ለ) ባሮክ
ሐ) ኤርሚያስ
መ) ዳንኤል
ለ) ባሮክ
በራዕይ መጽሃፍ መልዕክት ከተጻፈላችው ቤተ ክርስቲያናት መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ) ኤፌሶን
ለ)ፊልጵስዩስ
ሐ)ፊላደልፊያ
መ)ሰምርኔስ
ለ) ፊልጵስዩስ
ከካሌብ ጋር በቤተክርስቲያን ሙዚቃ እጫወታለሁ፤ አባቴ ፓስተር ነው፤ እኔ ማን ነኝ?
ፕሬዝ
የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን በተወሰደ ጊዜ ሊቀ-ካህን የነበረው ማን ነበር?
ሀ) ሳሙኤል
ለ)ሳዶቅ
ሐ)አቢያታር
መ)ኤሊ
መ)ኤሊ
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
ሀ) መዝ 91፡1
ለ)መዝ 19፡1
ሐ)መዝ 120፡1
መ)መዝ 34፡1
ሀ) መዝ 91፡1
ጳውሎስ የፊሊሞናን መልእክት የጻፈው ማንን አስመልክቶ ነው?
ሀ) ሉቃስ
ለ) አናሲሞስ
ሐ) ቲኪቆስ
መ) ቲቶ
ለ) አናሲሞስ
ዮሐንስ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ሲመለከት ያልተጠቀሰው ነገድ የቱ ነው?
ሀ)ሌዊ
ለ)ዳን
ሐ)ጋድ
መ)ምናሴ
ለ)ዳን
ከአዲስ ኪዳን መጻህፍት ሁለቱን ጽፌያለሁ፤ ከአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት መካከል አይደለሁም። እኔ ማነኝ?
ሉቃስ
የእግዚአብሔር ቤት በሚታደስበት ጊዜ የሕጉን መጽሐፍ አግኝቶ ሀግሪቱን ወደ መንፈሳዊ ትሀድሶ የመራው ንጉስ ማን ነው?
ሀ)ሕዝቅኤል
ለ)ሰለሞን
ሐ)ምናሴ
መ)ኢዮስያስ
መ)ኢዮስያስ
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
ሀ) ነህ 2፡20
ለ)ኢያ 1፡9
ሐ)ዕን 3፡18
መ)ዳን 12፡13
ሐ)ዕን 3፡18
የደቡቡን ይሁዳ ግዛት የተቆጣጠረው የባቢሎን ንጉስ ማን ነው?
ሀ)ዳርዮስ
ለ)ናቡከደናጾር
ለ)ቂሮስ
መ)ብልጣሶር
ለ)ናቡከደናጾር
በራዕይ መጽሃፍ ከተጠቀሱት ባርኮቶች አንዱ ያልሆነው የቱ
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው
ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው
በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው
የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ
ማቴ 5፡10
ራእይ 19፡9
ራዕይ 20፡6
ራዕይ 22፡7
ነቢዩ የበደለን ታሪክ ሲነግረኝ የፈረድበት ስል "ያ ሰው አንተ ነህ" አልኝ። እኔ ማን ነኝ?
ንጉስ ዳዊት
ሰለበረታ ልቡ በመታበዩ የተነሳ ፤ ወደ መቅደስ ገብቶ በዕጣን መሠዊያ ላይ በማጠን አምላኩንም እግዚአብሔርን የበደለው ንጉስ የቱ ነው?
ሀ)አሀዝ
ለ) ሕዝቅያስ
ሐ)ዖዝያ
መ)እዮሳፍጥ
ሐ)ዖዝያ
የሚከተለው ጥቅስ የት ይገኛል፡ "የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።"
ሀ)1ጢሞ 3፡16
ለ) ዮሐ 3፡16
ሐ)2ጢሞ 3፡16
መ) 1ዮሐ 3፡16
2 ጢሞቴዎስ 3፡16
ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ መቶውን ነቢያት ወስዶ በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው የነበርው ማን ነው?
ሀ) ኤልያስ
ለ)ኤልሳ
ሐ)አብድዩ
መ)ኢሳያስ
ሐ)አብድዩ
በራዕይ መጽሃፍ ዮሃንስ "በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም" የሚል ድምፅ የሰማው ሰለ የቱ ነው?
ሀ)ሰለ ሰባቱ ማህተም
ለ)ሰለ ሰባቱ ነገስታት
ሐ)ሰለ ሰባቱ ነጎድጓዶች
መ)ሰለ ሰባቱ ጽዋዎች
መ)
ሐ)ሰለ ሰባቱ ነጎድጓዶች
የኤማሁስ መንገደኞች ከሚባሉት ደቀመዛሙርት አንዱ ነኝ፤ እኔ ማን ነኝ?
ቀሊዮጳ
ኤርሚያስ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን መልዕክት የተጻፈበትን የብራና ጥቅልል ያቃጠለው ንጉስ ማነው?
ሀ)ኢዮአቄም
ለ)ኢዮስያስ
ሐ)ሴዴቅያስ
መ)ሕዝቅኤል
ሀ)ኢዮአቄም