ኢየሱስ የመጀመሪያው ተአምር፣ ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ በመቀየር የተከናወነው በዚህ ክንውን ነው።
የቃና ዘገሊላ ሰርግ
“ለሁሉም ጊዜ አለው” በሚለው ክፍሉ የሚታወቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የቱ ነው?
መክብብ
"ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት" ያለችው ማናት?
የማርያም እህት ማርታ
እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት የተሻገሩት ወንዝ ምን ይባላል።
ዮርዳኖስ ወንዝ
የኢየሱስ ሐዋርያት መካከል ስንት ወንድማማቾች አሉ? ሰማቸውን ጥቀስ?
ሁለት
ስምዖንና እንድርያስ
ዮሃንስና ያዕቆብ
ሁለቱን የእስራኤላውያን ሰላዮችን በመደበቅ ያዳነቻቸው በዚያም ምክንያት ከነቤተሰቧ የተረፈችው የኢያሪኮ ሴት ማን
ረሃብ
"ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ" ያለው ምነው?
ጴጥሮስ
ሐዋ 3፡6
እግዚአብሄር ያዕቆብን ወደዚህ ስፍራ ውጣ በዚያ ኑር ከወንድምህ ከኤሳው ፊት በሽሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠዊያ አድርግ። የተባለው በየትኛው ስፍራ ነው።
And God said unto Jacob, Arise, go up to this place, and dwell there: and make there an altar unto God
ቤቴል
በጳውሎስ መልዕክቶች ሰዉ ሁሉ ኃጢያተኛ መሆናቸውን ገልፆ የመዳኛውን መልዕክት በሰፊው ያብራራበት መልዕክት የትኛው ነው ?
ሮሜ
የእግዚአብሄርን ታቦት የተሸከሙት በሬዎች ሲፋንኑ ታቦቱ እንዳይወድቅ በእጁ በመደገፉ ምክንያት የተቀሰፈው ማነው
ዖዛ
ልጇ ቢሞትባትም “ሁሉ ነገር ደኅና ነው” ያለችው ሴት ማናት
ሱናማዊቷ ሴት
2 ነገሥት 4:26
ጳውሎስ ለሶስት ሰንበት የግዚአብሔርን ቃል እየጠከሰ ያስተማረበት በኃላም ሁለት መለዕክቶችን የላከበት የግሪክ ከተማ ማን ትባላላች
ተሰሎንቄ
ጴጥሮስ መላእኩ ከእስራት አስፈትቶት ወደቤት መጥቶብ በሩን ባንኳኳ ጊዘ ድምጹን አውቃ በሩን ግን ያልከፈተችለት ነግር ግን ወደ ውስጥ ገብታ በደጅ መኖሩን የተናገረችው የቤት ሰራተኛ ስም ማነው?
ሮዳ
ሐዋ 12፡12-14
ያየውን ሸክም በእግዚአበሔር ካቀረበ በኋላ እግዚአበሔር ክብሩን በማሳየት ሲመልስለት "እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።" ያለው ነቢይ ማን ይባላል።
I will rejoice in the LORD, I will be joyful in God my Savior.
ዕንባቆም
Habakkuk
"ይህ መታጠቂያ ያለውን ሰው አይሁድ በኢየሩሳሌም እንደዚህ ያስሩታል በአሕዛብም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል" ብሎ ትንቢት የተናገረው ነብይ ማነው?
አጋቦስ
ሐዋ 21፡ 10፟-12
መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ ያለውና ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ ያሰናበቱአቸው ከየት ነው።
አንጾኪያ
ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሄርም ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተፅፎዋል" የሚለው ክፍል በየትኛው መጽሃፍ ውስጥ ነው?
ዮሃንስ ወንጌል
ዮሃ 20፡31
እግዚአብሔር እርሱን ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ። ብሎ ትንቢት እንዲናገር የተሰጠው ለየትኛው ነብይ
Which prophet said “On the day when I act,” says the LORD Almighty, “they will be my treasured possession and I will spare them..."
ሚልክያስ
ሚል 3፡17
“እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም...” በማለት በምሬት የተናገረው ነብይ ማነው?
Which prophet of God said "O LORD, you deceived me, and I was deceived: you are stronger than I, and has prevailed: I am in derision daily, every one mocked me.
ነብዩ ኤርምያስ
ዝናብ በጠፋ ጊዜ ኤልያስን እንድትመግብ እግዚአብሄር ያዘጋጃት መበለት የምትኖርበት ከተማ የት ነው።
ሰራፕታ
1ነገ 17፡ 8